‎የኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ 4ኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታ የስታዲየም የመግቢያ ቲኬት አሻሻጥ ስርአት በተሻለ መንገድ ማቅረቡን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ታክ ቢዝነስ ግሩፕ አስታውቁ።

0
88

የፊታችን ማክሰኞ የሚደረገውን የኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ ጨዋታ ደጋፊዎች ሳይንገላቱ በቀላሉ ቲኬት ገዝተው ጨዋታውን የሚመለከቱበትን አሰራር አዘምኖ ቲኬቶችን በዲጅታል አሰራር ማቅረቡን ታክ ቢዝነስ ግሩፕ ለአሚኮ ገልጿል።

በዚህም የደጋፊዎችን እንግልት በመቀነስ በ10 ደቂቃ ውስጥ እስከ ስልሳ ሺህ ሰዎች ቲኬት መቁረጥ የሚያስችላቸውን አሰራር መዘርጋቱን አስታውቋል።
‎
‎መስከረም 19 ኢትዮጵያ እና ሴኔጋል ያደረጉትን ጨዋታ በስታዲየም ተገኝቶ ጨዋታውን ለመከታተል በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቲኬት ለመቁረጥ ቢፈልጉም በወቅቱ ስራ ላይ የዋለው የኦንላይን የቲኬት መሸጫ መተግበሪያ በተፈለገው ልክ አገልግሎት ባለመስጠቱ ተመልካቾችን ለእንግልት መዳረጉ ይታወሳል።

‎አሁን የተዘረጋው አሰራር ያንን ችግር በመቅረፍ በቀላሉ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል።
‎
‎የታክ ቢዝነስ ግሩፕ የቴክኖሎጅ ዳይሬክተር ጸጋ ሰሎሞን ለአሚኮ በሰጠው ሀሳብ የኦንላይን ቲኬት አሻሻጡ ስማርት ስልክም ይሁን የበተን ስልክ ያላቸው ተጠቃሚዎች በቀላሉ ቲኬት መቁረጥ የሚችሉበት መተግበሪያ ሲሆን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ድረ ገጽ በመግባት መቁረጥ እንደሚቻል አስረድተዋል።
‎
‎የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተወካይ አቶ አምሃ ተስፋዬ በበኩላቸው ለማክሰኞው ጨዋታ የባለፈው ችግር እንደማይደገም አብራርተው በታክ ቢዝነስ ግሩፕ የተዘጋጀው የቲኬት መሸጫ መተግበሪያ ቀላል ምቹና ፈጣን በመሆኑ ማንኛውም ሰው ባለበት ሆኖ ቲኬት መቁረጥ የሚያስቸለው ነው ብለዋል።

በመሆኑም ተመልካቾች ያለ ስጋት የሚፈልጉትን አይነት ቲኬት ገዝተው የብሄራዊ ቡድኑን ጨዋታ መታደም እንደሚችሉ ጨምረው አስረድተዋል።
‎
‎የኢትዮጵያ እና የሞዛምቢክ ጨዋታን ለመታደም የመግቢያ ቲኬቶች እንደ ደረጃቸው ባለ 100፣200 እና 500 ዋጋ እንደተተመነላቸው ተነግሯል።

የቲኬት ሽያጩ ከኦላይን በተጨማሪ ከጨዋታው አንድ ቀን አስቀድሞ የፊታችን ሰኞ እና ማክሰኞ በእጅ በጅ ሽያጭ እንደሚከናወንም ታውቋል።
‎
‎ተመልካቶች የመግቢያ ቲኬቶችን ሲገዙ የስታዲየም የመግቢያ በሮች ቁጥር የገዙት ቲኬት ላይ የተገለጸ በመሆኑ ለደንብ አስከባሪዎችም ይሁን ለጸጥታ አካላየት ሊፈጠር የሚችለውን ጫና በመቀነስ በኩል ታላቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here