ሊቨርፑል ውሌን ለማራዘም ከፈለገ በክለቡ መቆየት እፈልጋለሁ – አሊሰን ቤከር

0
75

 

የ34 ዓመቱ የሊቨርፑል እና የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ በክለቡ ያለው ቆይታ በዚህ የውድድር ዓመት ይጠናቀቃል።

የውል ማራዘም ጉዳይ በክለቡ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ እንደሆነ የገለፀው ግብ ጠባቂው እርሱ ግን ለተጨማሪ ጊዜ መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሯል።

ዋንጫዎችን ለማሸነፍ እና ጥሩ የሆነ ብቃት ለማሳየት ጠንክሮ እደሚሰራም ገልጿል።

አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራዮላ አሊሰን በሊቨርፑል ለተጨማሪ ዓመታት ሊቆይ እንደሚችል ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

ባለፈው ዓመት ከጁቬንቱስ ጋር ስሙ በስፋት ሲያያዝ የነበረው አሊሰን በሊቨርፑል መቆየትን ምርጫው አድርጓል።

አሊሰን በ2018 ከሮማ በ66.8 ሚሊዮን ፓውንድ ሊቨርፑልን ከተቀላቀለ በኋላ 347 ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል።

መሀሪው አወቀ(ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት የተግባር ተለማማጅ)

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ህዳር _01_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here