ለሜዳልያ የሚጠበቁት ኤልሳቤጥ አማረና ዮሚፍ አበበ

0
95
**************
የዳካር ወጣቶች ኦሎምፒክ መከናወኑን ሲቀጥል የአትሌቲክስ ውድድሮች ዛሬ በሚደረጉ በርከት ያሉ ፉክክሮች ይጠናቀቃሉ፡፡ ትላንት ኢትዮጵያ በተካፈለችባቸው 4 የፍጻሜ ውድድሮች 3 የወርቅና 1 የብር ሜዳልያ መመዝገቡ ይታወሳል፡፡
ዛሬ ደግሞ በሴቶች 1500 ሜትርና በወንዶች 800 ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለሜዳልያ ይፋለማሉ፡፡ ኤልሳቤጥ አማረ በ1500 ሜትር ከ13 አትሌቶች ጋር ስትፎካከር ፈጣን ሰአት በመያዝ ጭምር ነው፡፡
4 ደቂቃ ከ01 ሰከንድ ከ32 ማይከሮ ሰከንድ በማያዝ ከሌሎቹ በተሻለ በቀዳሚነት ተቀምጣለች፡፡ በወንዶች 800 ሜትር በትላንትናው እለት በነበረው ማጣሪያ በምድብ 2 ሁለተኛ በመውጣት ማለፉን ያረጋገጠው ዮሚፍ አበበ ከኬንያና ዩጋንዳ አትሌቶች ከፍተኛ ፉክክር ይጠብቀዋል፡፡
ከትላንቱ ማጣሪያ በኋላ አስተያየቱን የሰጠው ዮሚፍ የወርቅ ሜዳልያ ለማምጣት መሙ ላይ እሰየማለሁ በማለት ለድል መራቡን አረጋግጧል፡፡
ውድድሩም ምሽት 2 ሰዓት ከ 5 ላይ ይደረጋል፡፡
ሐናማርያም መስፍን
#ባሕር_ዳር #ህዳር _01_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here