በመጀመሪያው ቀን በተካሄዱ በወጣት ሴቶች 10.2 ኪሎሜትር የግል ሰአት ሙከራ የብስክሌት ውድድር ራሄል ጊምባቶ እንዲሁም 20.4 ኪሎሜትር በሸፈነው የግል ሰአት ሙከራ ከ23 ዓመት በታች ደግሞ ፅጌ ካህሣይ በተመሳሳይ የነሀስ ሜዳልያን አስገኝተዋል፡፡
ውድድር ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት ሲቀጥል ኢትዮጵያውያን ብስሌተኞች የሚሳተፉባቸው ዘርፎች ነገ ይከናወናሉ፡፡
በወጣት ሴቶች የጎዳና ላይ ውድድር ራሄል ጊምባቶና ቅሳነት ገብረስላሴ የሚካፈሉ ይሆናል፡፡
68.8 ኪሎሜትር በሚሸፍነው ርቀት በመክፈቻው እለት የነሀስ ሜዳልያና ዲፕሎማ ያመጡት ራሄልና ቅሳነት ለሌላ ድል ይፎካከራሉ፡፡
ነገ የምንሳተፍበት ሌላኛው ዘርፍ የወጣት ወንዶች 119.8 ኪሎሜትር በሚሸፍነው ነው፡፡
ያሬድ ካህሳይና አቢይ መብራቱ በወንዶቹ ዘርፍ የኢትዮጵያን የመጀመሪያ ሜዳልያ ለማስመዝገብ ይገባሉ፡፡
ሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



