የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ2019 የውድድር አመት እሁድ ይጀምራል።

0
101

 

ሶስት ጊዜ ከመራዘም በኋላ ፕሪሚየር ሊጉ በእለተ እሁድ ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለታል።

14 ክለቦችን የሚያሳትፈው ይሄው የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ከጥቅምት 15 እስከ ጥር 18 ድረስ ይካሄዳሉ።

የዘንድሮው ውድድር ከአመታት በኋላ ክለቦቹ በሜዳቸው እና ከሜዳቸው ውጭ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ መሆኑ ከተመልካች የራቀውን የሴቶች ሊግ ወደ ሜዳ የሚመልስ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ አስራ አራቱም ተሳታፊ ክለቦች ሴት አሰልጣኞች ያካተቱበት ውድድር በመሆኑ የዘንድሮውን ልዮ ያደርገዋል።

በመጀመሪያ ሳምንትም የአማራ ክልል ብቸኛው ተወካይ ባህርዳር ከነማ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ ወደ ሀዋሳ አቅንተው በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ከሀዋሳ ከተማ ጋር እሁድ 8ሰአት ላይ ይጫዎታሉ።
የጊዮን ንግስቶቹ ቀደም ብለው ቅድመ ዝግጅታቸውን አዲስ አበባ ላይ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

12 አዳዲስ ተጫዋቾችን ከነባሩ ስብስብ ጋር በማዋሀድ የወዳጅነት ጨዋታ አድርገው ራሳቸውን ፈትሸው ነው ወደ ሀዋሳ ያቀኑት ።

በዳናይት ሲሳይ

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_13_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here