ዴቪድ ሲልቫ ከጡረታ ተመልሶ የሆንግ ኮንግ ክለብን ተቀላቀለ።

0
13
የስፔን እና የማንቸስተር ሲቲ የቀድሞ አማካይ ዴቪድ ሲልቫ የሆንግ ኮንግ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ የኾነውን ሱፕሪም ሻ ቲን ተቀላቅሏል።
የ40 ዓመቱ የስፔን እግር ኳስ ኮከብ ከክለቡ ጋር ሁሉንም ሕጋዊ የዝውውር ሰነዶች መፈረሙ ተረጋግጧል።
በአስደናቂ የኳስ ቁጥጥሩ እና የጨዋታ ብቃቱ አስማተኛው በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ሲልቫ፣ በጨዋታ ዘመኑ ካስመዘገባቸው ውጤቶች
መካከል ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር 1 የዓለም ዋንጫ እና 2 የአውሮፓ ዋንጫዎች፤ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር 4 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ
ዋንጫዎችን፣ ጨምሮ 2 ኤፍ ኤ ካፕ ፣ 5 የሊግ ካፕ እና 3 የኮሚዩኒቲ ሺልድ እንዲሁም በስፔን 2 የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫዎችን አሳክቷል።
ይህ አንጋፋ ተጫዋች ከእግር ኳስ ጡረታ በኋላ እንደገና በ40 ዓመቱ ወደ ሜዳ መመለሱ የእግር ኳስ አፍቃሪዎችን ትልቅ ትኩረት ስቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here