ዴዚሪ ዱዌ ለረጅም ጊዜ ከሜዳ የሚያርቅ ጉዳት ገጠመው።

0
30

የፓሪስ ሴንት ዠርሜን የፊት መስመር ተጫዋች የኾነው ዴዚሪ ዱዌ በጉልበቱ ላይ በደረሰበት ከባድ ጉዳት ምክንያት ለበርካታ ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ ይፋ አድርጓል።

ዱዌ ትናንት ምሽት ፓሪሰን ዠርሜ ኒስን 3 ለ 2 ባሸነፈበት ጨዋታ የጉልበት ጅማት መበጠስ ጉዳት አጋጥሞታል።

ከጉዳቱ ለማገገም ዘጠኝ ወራት የሚፈጅ በመኾኑ የ21 ዓመቱ ፈረንሳዊ ተጫዋች በቀሪው የውድድር ዓመት ዳግም ወደሜዳ የመመለስ ዕድሉ ጠባብ ኾኗል።

ይህም ክለቡ ለረጅም ወራት ከሚያገኛቸው ተጫዋቾች መካከል ከኽቫቺ ቅቫራስሄሊያ በመቀጠል ሁለተኛው ተጫዋች ኾኗል።

በዚህ ወር መጨረሻ ቀዶ ሕክምና እንደሚያደርግም ይጠበቃል።

#በሐናማርያም_መስፍን

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#አዲስ_አበባ #ኅዳር_13_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here