ካፍን ከገንዘብ ቀውስ ያወጣው የፓትሪስ ሞትሲፔ አመራር።

0
19

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ 48ኛ ጠቅላላ ጉባኤው በናይጀሪያ አቡጃ ተካሂዷል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ በፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ (ዶ.ር) አመራር ወደ ፋይናንሳዊ መረጋጋት መመለሱ፣ በናይጄሪያ አቡጃ በተካሄደው 48ኛው የካፍ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ይፋ በተደረገው የ2026 ዓመታዊ የፋይናንስ ሪፖርት ተንጸባርቋል።

ወደ ትርፋማነት መመለስ፣ የተሻሻሉ ክምችቶች እና ጠንካራ የጥሬ ገንዘብ አቋም፤ ካፍ የአፍሪካ እግር ኳስን ልማት እና ዕድገት ማስፋፋትን ለመቀጠል የሚያስችል ይበልጥ ዘላቂ የፋይናንስ መሠረት ይሰጡታል ተብሏል በጉኤው።

ከአምስት ዓመታት በፊት ካፍ ከ100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ዕዳ ውስጥ ገብቶ በከባድ የገንዘብ ቀውስ ውስጥ እንደነበር ይታወሳል።

ባለፉት አምስት ዓመታት ተግባራዊ የተደረገው እና በካፍ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፓትሪስ ሞትሴፔ የተመራው የለውጥ ስትራቴጂ ካፍን ራስን ወደ ማስቻል መንገድ አምጥቶታል።

ዛሬ ካፍ የ31 ነጥብ 2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን በዓመታዊ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። የካፍ አጠቃላይ ገቢ ከ200 በመቶ በላይ ዕድገት በማሳየት ወደ 284 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከፍ ብሏል።

የካፍ ክምችቶችም ከ16 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር ጉድለት ወደ 14 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር አዎንታዊ አቋም በማሸጋገር ከፍተኛ መሻሻል አሳይተዋል፤ የጥሬ ገንዘብ ደግሞ የበጀት ዓመቱ ማብቂያ በኾነው ሰኔ 2026 መጨረሻ ላይ 118 ነጥብ 8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል።

የ2026 የበጀት ዓመት ማብቂያ ከታየው የተሻሻለ የፋይናንስ አቋም ባሻገር፣ ካፍ ለአባል ማኅበራቱ፣ ለዞን ማኅበራት፣ ለክለቦች እና ለውድድሮች የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል።

በዚህም ኢትዮጵያን ጨምሮ 54 አባል ሀገራት በየዓመቱ 170 ሚሊዮን ብር ከካፍ ድጋፍ ያገኛሉ::

#በቴዎድሮስ_ኃይለኢየሱስ

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#አዲስ_አበባ #ኅዳር_13_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here