የዓለማችን ምርጥ የግራ መስመር ተከላካዮች ተርታ እየተቀላቀለ የሚገኘው ጣሊያናዊው ኮከብ ሪካርዶ ካላፊዮሪ።

0
9
የአርሰናል እና የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን የግራ መስመር ተከላካይ ሪካርዶ ካላፊዮሪ በክለቡም ኾነ በብሔራዊ ቡድኑ እያሳየ የሚገኘው አስደናቂ ብቃት የእግር ኳስ ተንታኞችን እና ደጋፊዎችን ቀልብ መሳቡን ቀጥሏል።
ጣሊያን በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ቱርክን 3 ለ 1 በረታችበት ጨዋታ ላይ ግብ ማስቆጠር የቻለው ካላፊዮሪ ለሀገሩ ባደረጋቸው ያለፉት 9 ጨዋታዎች 4 የግብ እና 4ግብ የሚኾኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ማስመዝገብ ችሏል።
ይህ ለግራ መስመር ተከላካይ እጅግ አስደናቂ የማጥቃት ብቃት ነው። በአሁኑ ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉ ምርጥ የግራ መስመር ተከላካዮች አንፃር ሲመዘን ካላፊዮሪ በመሪዎቹ ተርታ ይገኛል፡
ካላፊዮሪ በአርሰናል እና በጣሊያን ብሔራዊ ቡድን የሚያሳየው ወጥ የኾነ ማጥቃት እና ታክቲካዊ ተለዋዋጭነት በአሁኑ ወቅት ከዓለማችን ከአምስቱ ምርጥ የግራ መስመር ተከላካዮች ተርታ እንዲመደብ አስችሎታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here