የማንችስተር ዩናይትድ እና የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አማካይ የኾነው ብሩኖ ፈርናንዴስ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር ስለነበረው ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ አስተያየቱን ሰጥቷል።
ብሩኖ ፈርናንዴስ ከሮናልዶ ጋር መነጋገሩን ገልጾ፣ ሮናልዶ የብሔራዊ ቡድኑ እና የሀገሪቱ የዘላለም ታላቅ አርማ መኾኑን እንደነገረው አስታውሷል።
“እሱ ለእኛ ሁልጊዜም ከሁሉ በላይ ትልቁ ሰው ኾኖ ይኖራል” ብሏል።
በተጨማሪም የብሔራዊ ቡድኑ አባላት የተከፋፈሉ ሳይኾኑ ሙሉ በሙሉ የተባበሩ መኾናቸውን አጽንኦት ሰጥቶ ተናግሯል።
ቡድኑ በውጭ ወሬዎች ሳይከፋፈል በአንድነት እንደሚቀጥልም ጠቁሟል።
አለመግባባቶች በውስጥ መፈታት እንዳለባቸው እና ለሁለቱም ወገኖች በሚመች መልኩ በጥሩ ሁኔታ መጠናቀቅ እንደሚገባቸው አሳስቧል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከእግርኳስ ታላላቆች ጎን ለጎን በሁሉም ፖርቹጋላውያን ልብ ውስጥ ሁልጊዜም የማይነካ ልዩ ቦታ እንዳለው በመግለጽ መልዕክቱን አስተላልፏል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_23_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



