ቲየሪ ኦንሪ ለብራድሊ ባርኮላ ደጋፊዎቹ እስኪላመድ ጊዜ እንዲሰጡት ጥሪ አቀረበ።

0
9
የቀድሞው የፈረንሳይ እና የአርሰናል እውቁ አጥቂ ቲየሪ ኦንሪ፣ ደጋፊዎች በ123 ሚሊዮን ዩሮ ዝውውር ሊቨርፑልን ለተቀላቀለው ወጣቱ አጥቂ ብራድሊ ባርኮላ ጥሩ አቀባበል እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርቧል።
ኦንሪ እንደገለጸው ባርኮላ አዲስ ወደ ሊቨርፑል የመጣ እንደመኾኑ መጠን ከቋንቋው በተጨማሪ የሊጉ የጨዋታ ስልት እና የፉክክር ጥንካሬ የተለየ በመኾኑ ለመላመድ ጊዜ ያስፈልገዋል ነው ያለው።
“ቦታው ለመጀመር ቀላል አይደለም፤ የተከፈለው ከፍተኛ የዝውውር ዋጋም ጫና ሊኾንበት ይችላል” ያለው ኦንሪ፣ “ነገር ግን ካለው ብቃት አንጻር እና በፍጥነቱ ረገድ ምን ያህል አደገኛ እንደኾነ ሁላችንም እናውቃለን” ሲል አክሏል።
ኾኖም በዘመናዊ እግር ኳስ ሰዎች ከተጫዋቾች ውጤት ከመጠበቅ አንጻር ሙሉ በሙሉ እስኪላመድ ድረስ ረጅም ጊዜ እንደማይጠብቁት የጠቆመው ኦንሪ፣ ባርኮላም በፍጥነት ራሱን አብቅቶ ውጤት ማሳየት እንደሚጠበቅበት ለኤስቢሲ ተናግሯል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here