ቴን ሀግ በታክቲክ ጎበዝ፤ በቡድን አያያዝ ግን ጥሩ አልነበረም።

0
11
የቀድሞው የማንቼስተር ዩናይትድ አማካኝ ፍሬድ በቻርላ ቦድካስት ላይ በሰጠው አስተያየት የቀድሞ አሠልጣኙን ኤሪክ ቴን ሀግን አድንቆ ጠንከር ያለ ትችትም ሰንዝሮባቸዋል።
ስለ ታክቲክ ብቃታቸው ሲናገርም “በታክቲክ በኩል እጅግ ጎበዝ እና እስካሁን ካገኘኋቸው አሠልጣኞች መካከል ከምርጦቹ አንዱ ነው” ብሏል።
የቡድን አያያዝን በተመለከተ “ከቡድኑ ጋር ያለው ግንኙነት ግን ጥሩ አልነበረም፤ ከሁሉም ተጫዋች ጋር ይጣላ ነበር” ሲል ገልጿል።
“ከእኔ፣ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ከካሴሚሮ እና ከራሽፎርድ ጋር አለመግባባቶች ነበሩት” ሲል የነበረውን የቡድን ሁኔታ ተናግሯል።
አሰላለፍ ላይ አሠልጣኙ ለሀገሩ ተጫዋቾች ያደላ እንደነበር ገልጾ “የኔዘርላንድ ተጫዋቾች ብቻ ዕድሉን ያገኙ ነበር” ሲል ተናግሯል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here