የቀድሞው የባርሴሎና፣ የአሁኑ የፓሪስ ሴንት ዠርመን (ፒኤስጂ) የክንፍ ተጫዋች ኦስማን ዴምቤሌ በካታሎኑ ክለብ በነበረው ቆይታ ከተመለከታቸው ድንቅ ተጫዋቾች መካከል ሊዮኔል ሜሲን ለየት አድርጎ አድንቋል።
ዴምቤሌ በሰጠው አስተያየት፦ “በባርሴሎና በነበርኩባቸው ዓመታት በርካታ ልዩ እና ድንቅ ተጫዋቾችን ተመልክቻለሁ፤ ነገር ግን ‘ፍጹም’ የነበረው ሜሲ ነው” ብሏል።
አክሎም ከሜሲ አርዓያነት በመነሳት የተሟላ ተጫዋች መኾን እንደሚፈልግ ሲገልጽ፦ “እኔም ግብ በማስቆጠር፣ ለግብ የሚኾኑ ኳሶችን በማመቻቸት እና ቡድኑን በሁሉም ረገድ በመርዳት የተሟላ ተጫዋች መኾን እፈልጋለሁ” ሲል ለማርካ ተናግሯል።
#Dembélé #Messi #Barcelona #PSG #FootballNews
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_23_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



