ትዕግስት አሰፋ እና ጉዩ አዶላ በበርሊን አሸነፉ።

0
66

 

52ኛው የበርሊን ማራቶን ዛሬ ተካሂዷል ፡፡ ኢትዮጵያ በሁለቱም ፆታ አሸናፊ ሆናለች፡፡

በወንዶቹ ጉዩ አዶላ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ጉዩ ከሌሎች ሯጮች ተነጥሎ ቀድሞ በመውጣት ጥሩ አጨራረስ በማሳየት ነው ያሸነፈው፡፡

ርቀቱን 2፡02፡51 በሆ ሰአት ሲያጠናቅቅ ሌላኛው የሃገሩ ልጅ ገመቹ ዲዳ 02:03:51በመግባት ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡

በርሊን ማራቶንን ጉዩ አዶላ ለ2ኛ ጊዜ ያሸነፈበት ሆኗል። በወንዶች ከ4ኛ እስከ 8ኛም ኢትዮጵያውያን ተከታትለው ገብተዋል።

በሴቶቹ በርቀቱ ተጠብቃ የነበረችው ትግስት አሰፋ አሸናፊ ሆናለች፡፡

ትእግስት ክብረወሰኑን የምትሰብርበት እድል እጇ ላይ ቢሆንም ከ40 ኪ.ሜ በኋላ በገጠማት ጉዳት ሳይሳካላት ቀርቷል። ከጉዳቷ ጋር ታግላ ነው ያሸነፈችው፡፡

ትግስት አሰፋ 2፡ 11 ፡04 በመግባት የግል ምርጥ ስዓቷን ጭምር በማሻሻል አሸንፋለች።

ጀግናዋ አትሌት ከባዱን ጉዳት ተቋቁማ በበላይነት ብታጠናቅቅ ሪከርዱን ግን ሳታሻሽል ቀርታለች።

ሌሎች ኢትዮጵያውያን በዳቱ ሂርፓ፣ ደራ ዲዳ በቀለች ጉደታ እና አለሚቱ ታሪኩ እስከ 5ኛ ተከታትለው ገብተዋል። እስከ 10ኛ ከወጡት መካከል 7ቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ዳናይት ሲሳይ

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_17_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here