በላሚን ያማል ሃሳብ ምን ያክሎቻችን እንስማማ ይኾን?

0
92

 

ላሚን ያማል “እኔ እግር ኳስ የምጫወተው ለገንዘብ ሳይኾን ለኳስ ፍቅር ነው” ብሏል።

የባርሴሎና እና የስፔን ብሔራዊ ቡድን ወጣት ኮከብ ላሚን ያማል ለእግር ኳስ ያለው ፍቅር ከገንዘብ በላይ መኾኑን ገልጿል።

ያማል ከዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ እንደተናገረው፣ በሜዳ ላይ የሚያሳየው ድንቅ ብቃት የመነጨው ለጨዋታው ካለው ጥልቅ ፍቅር እና ደስታ እንጅ ለገንዘብ አይደለም ብሏል።

“በግብ ወይም ለግብ አመቻችቶ መስጠት ላይ ብቻ የተጠመዱ ተጫዋቾች በጨዋታው በትክክል አይደሰቱም” ሲል አነጋጋሪ ሃሳብ ሰጥቷል።

“እኔ የምጫወተው ለመዝናናት እና እስካሁን ያላገባን የቡድን አጋሬን በማገዝ ግብ እንዲያስቆጥር በማድረግ ደስታን ለመፍጠር ነው” ብሏል

ወጣቱ ያማል በባርሴሎና እና በስፔን ብሔራዊ ቡድን ውስጥ እያሳየ ያለው ድንቅ ብቃት በዓለም እግር ኳስ ትልቅ ትኩረትን የሳበ ሲኾን ይህ የጨዋታ ፍልስፍናው ደግሞ በደጋፊዎች ዘንድ የበለጠ አድናቆትን አትርፎለታል።

አንዳንድ የስፖርት ቤተሰቦች ግን በሀሳቡ እንደማይስማሙ ጋዜጣው አስነብቧል። እርሰዎስ በሃሳቡ ይስማሙ ይኾን?

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_17_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here