የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን የፊታችን ማክሰኞ መስከረም 19/2019 ዓ.ም ለማካሄድ ዛሬ አመሻሹ ላይ ባሕር ዳር ገብቷል።
በመጀመሪያ ጨዋታቸው በሱዳን 1 ለ 0 የተረቱት ዋልያዎቹ፣ የፊታችን ማክሰኞ በባሕር ዳር ስታዲየም ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር ይጫወታሉ።
ሴኔጋል በመጀመሪያ ጨዋታዋ ከሞዛምቢክ ጋር 1 ለ 1 አቻ ስትለያይ፣ ምድቡን ሱዳን በ3 ነጥብ እየመራች ትገኛለች።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_16_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ዋሊያዎቹ ባሕር ዳር ገብተዋል



