በአለም አትሌቲክስ የኢላይት ደረጃ ከተሰጣቸው የ10 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሮች መካካል በሮማኒያ የሚከናወነው የቲራንስልቫኒያ 10 ኪሎሜትር ውድድር ነው፡፡
ቢዘህ መድረክም ኸይሪ በጂጋ በድጋሜ የማሸነፍና የቦታውን ክብረወሰን የማሻሻል ከፍተኛ ግምትን አግኝቷል፡፡
ውድድሩ ከተጀመረበት 2021 ጀምሮ በተደረጉ 5 መድረኮች በሁለቱም ጾታ 4ቱ የተጠናቀቁት በኬንያውያን አትሌቶች የበላይነት ነው፡፡
ያለፈው አመት 2025 ላይ ግን ኢትዮጵያዊያኖቹ ኸይሪ በጂጋና መዲና ኢሳ አሸናፊ በመሆን ቀዳሚ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡
ኸይሪ በጂጋ 2025 ላይ ሲያሸንፍ 26 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ ሲሆን ይሄም ከአለማችን ፈጣን ሰአቶች መካከል ሆኖለታል፡፡
በውድድሩ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው ወጣቱ አትሌት ሮማንያ ላይ በድጋሜ ለማሸነፍና የቦታውን ክብረወሰን ለመስበር በመጪው እሁድ ጥቅምት 4/2019 ወደ ብራሾቭ ከተማ ይመለሳል።
በአሁን ወቅት ኸይሪ በጂጋ የግል ሰዓቱን ወደ 26 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ በመቀነስ ማሻሻል ችሏል።
ይህ ደግሞ በሮማኒያ ታሪክ ፈጣኑ የ10 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ውድድር ሰዓት በብራሾቭ ሊመዘገብ እንደሚችል ትልቅ ተስፋን ፈጥሯል።
በፈረንሳይዋ ሊል ለመጨረሻ ጊዜ በጎዳና ላይ ውድድር የተካፈለው ኸይሪ በጂጋ ባለፈው ወር በሎዛን ዲያመንድ ሊግ የ5000 ሜትር መም ውድድር 9ነኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ ፈጣን ሰአቱን ወደ 13 ደቂቃ ከ03.27 ሰከንድ ማሳደግ ችሏል።
የውድድሩ ዳይሬክተር ዳንኤል ሳንታ እንደገለጹት ይህ ውድድር ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ነው፡፡ ፈጣን ሰዓት ማስመዘገብ የሚፈልግ አትሌት መምጣት ያለበት ወደዚህ ነው።» በማለት በልበ ሙሉነት ተናግረዋል።
የቦታው ክብረወሰን 26 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ ሲሆን በ2022 በኬንያዊው አትሌት ኒኮላስ ኪሜል ያስመዘገበውም ነው፡፡
ከዚህ በ3 ሰከንዶች ብቻ የሚዘገየው ፈጣኑ አትሌት ኸይሪ በጂጋ ቢሆንም ከእሱ ጋር ለመፎካከር ከ27 ደቂቃ በታች ማስመዝገብ የቻሉ ሌሎች 4 አትሌቶች ይሳተፋሉ።
ከነዚህም መካከል ባለፈው ዓመት ከኸይሪ ጋር እስከመጨረሻው ሜትር ድረስ አስደናቂ ትንቅንቅ አድርጎ የተሸነፈው የደቡብ አፍሪካው ማክስሜ ቻውሜቶን እና የኬንያው ሲላስ ሴንቹራ ይጠቀሳሉ።
ጌትነት ዋለና ኩማ ግርማ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ተሳታፊ ናቸው፡፡
የዘንድሮው ውድድርም በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች በቀጥታ ይተላለፋል። የሴቶች አትሌቶች ዝርዝር ደግሞ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



