የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ዛሬ አንድ ብለው መካሄድ ይጀምራሉ፡፡

0
87

 

በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ኬኒያ፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ የጣምራ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ 48 የአፍሪካ ሀገራት በ12 ምድቦች ተከፍለው ይፎካከራሉ።

በየምድቡ 6 ጨዋታዎች ተደርገውም 24 አላፊ ሀገራት በቀጣይ ዓመት ለሚካሄደው ውድድር ይለያሉ፡፡ ዛሬም ስምንት ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡

ኮትዲቯር ጋናን የምታስተናግድበት የምድብ ሦሥት ጨዋታ ከዛሬ ጨዋታዎች መካከል ትኩረት ያገኘው መርሐግብር ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ 10 ከሴኔጋል፣ሞዛምቢክ እና ሱዳን ጋር ተደልድሏል።

ዋሊያዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ነገ መሥከረም 15/2019 ዓ.ም ምሽት 1፡00 ላይ ከሱዳን ጋር ደቡብ ሱዳን ላይ ያደርጋሉ፡፡

በመጭው ማክሰኞ መሥከረም 19/2019 ዓ.ም ደግሞ ባሕር ዳር ላይ ሴኔጋልን ያስተናግዳሉ፡፡

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_14_2019_ዓ_ም

ሰኢድ ኢብራሂም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here