ዌይን ሩኒ በማንቸስተር ዩናይትድ ላይ የሰጠው አነጋጋሪ አስተያየት።

0
136

 

ዌይን ሩኒ «አብዛኞቹ የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች ብቁ አይደሉም» ሲል የሰጠው ሃሳብ የስፖርት ቤተሰቡን እያነጋገረ ይገኛል።

የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ዌይን ሩኒ በክለቡ ተጫዋቾች የአመለካከት እና የብቃት ማነስ ላይ ጠንካራ ትችት ሰንዝሯል።

ሩኒ ስለ ተጫዋቾቹ ብቃት ሲናገር፦ «ተጫዋቾቹ ለክለቡ ብቁ ናቸው ወይ? አብዛኞቹ አይደሉም» ብሏል።

አክሎም «እኔ ለማንቸስተር ዩናይትድ በምጫወትበት ወቅት ቡድኑ በሩጫ እና በትግል ከሊጉ እጅግ ድንቅ ነበር» ያለው ሩኒ፤ «አሁን ተጫዋቾቹን ስመለከት የስብዕና፣ የዕውቀት፣ የመታገል እና ለክለቡ የመቆርቆር ስሜት እጥረት ይታይባቸዋል» ሲል ከኢኤስፒኤን ጋር ባደረገው ቃለመጠይቅ ቅሬታውን ገልጿል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_14_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here