ከ17 ቀናት በኋላ በሚጀመረው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር፣ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የተደለደለበት ምድብ ዛሬ ይፋ ኾኗል።
ዛሬ ይፋ በተደረገው የምድብ ድልድል መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሦሥት ሀገራት በሚገኙበት ምድብ ሁለት የተደለደለ ሲኾን በምድቡም ከዩጋንዳ እና ከቡሩንዲ ጋር ይፎካከራል።
የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ውድድሩ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 09 ድረስ በሩዋንዳ ኪጋሊ ከተማ የሚካሄድ ይኾናል።
በዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



