ሊዮኔል ሜሲ በመጨረሻው የብሔራዊ ቡድን ጨዋታው ልዩ ማሊያ ሊለብስ ነው።

0
91

 

የአርጀንቲናው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ለብሔራዊ ቡድኑ በመጨረሻው ጨዋታ ላይ የሚለብሰውን ልዩ ማሊያ በቪዲዮ አስተዋውቋል።

ሜሲ የፊታችን መስከረም 20 አርጀንቲና ከቤኒን ጋር በምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ 208ኛውን እና የመጨረሻ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን ያደርጋል።

የ39 ዓመቱ የአርጀንቲናውያን ኩራት ሜሲ ይህን ልዩ ማሊያ ሲያስተዋውቅ «አንድ የመጨረሻ ጨዋታ፤ ለዘላለም የምትቀር ማሊያ» የሚል መልዕክት አጅቦታል።

ሊዮኔል ሜሲ እስካሁን ለአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በተሰለፈባቸው 207 ጨዋታዎች 125 ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሲኾን ከሀገሩ ጋር የዓለም ዋንጫን እና የኮፓ አሜሪካ ዋንጫዎችን ማሰካት ችሏል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_12_2019_ዓ_ም

በዳናይት ሲሳይ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here