የስፔኑ የሬዲዮ ጣቢያ ኮፔ ባወጣው ዘገባ በሪያል ማድሪድ እና አትሌቲኮ ማድሪድ መካከል የተደረገውን የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ የመሩት ዳኛ አልቫሮ ኦርቲዝ አሪያስ ቢያንስ ለቀጣዮቹ ሁለት የላሊጋ ጨዋታዎች ከዳኝነት እንዲገለሉ ሊደረግ መኾኑን አስነብቧል።
ሪያል ማድሪድ በደርቢው ጨዋታ ከተሰጡ የዳኝነት ውሳኔዎች ጋር ተያይዞ በዳኛ ኦርቲዝ አሪያስ አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እና ጠንካራ ተቃውሞ አቅርቧል።
አትሌቲኮ ማድሪድ በበኩሉ በዳኞች ላይ የሚሰነዘሩ ቅሬታዎች እና ትችቶች ወሰን ማለፍ የለባቸውም ሲል አሳስቧል።
የላሊጋው የዳኞች ኮሚቴ የውሳኔውን ስህተቶች በመገምገም ዳኛ ኦርቲዝ አሪያስን ቢያንስ ለሁለት የሊግ ጨዋታዎች ከዳኝነት ለማገድ መወሰኑ ተገልጿል።
በጨዋታው አትሌቲኮ ማድሪድ ሪያል ማድሪድን 2ለ1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_12_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



