የማንቼስተር ሲቲ ድንቅ ጅማሮ ይዘልቅ ይኾን?

0
83

 

ማንቼስተር ሲቲ በ2026/27 የውድድር ዘመን ድንቅ ጅምር አድርጓል።

ማንቼስተር ሲቲ በ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን በጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ 5 ጨዋታዎች ሁሉንም በማሸነፍ 15 ነጥብ በመሠብሠብ የሊጉ ሰንጠረዥ መሪ መኾን ችሏል።

ይህ ስኬት ከተመሳሳይ የ2025/26 የውድድር ዘመን ጅምር ጋር ሲነጻጸር የ8 ነጥብ ብልጫ ያለው ሲኾን፣ ቡድኑ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ የመጀመሪያ 5 ጨዋታዎች መሠብሠብ የቻለው 7 ነጥብ ብቻ ነበር።

ቡድኑ ባሳየው ፍጹም የውጤታማነት ጉዞ የአዲሱን የውድድር ዘመን የዋንጫ ፉክክር በከፍተኛ የበላይነት ከመምራቱም በላይ የዋንጫው ተስፋ በእጁ እንዳለ የሚያመላክት እንደኾነ ስካይ ስፖርት አስነብቧል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_12_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here