ለእግር ኳሱ ኮከብ ሜሲ በካምፕ ኑ የተነፈገው ክብር ሊመለስ ነው።

0
103

 

የባርሴሎናው ፕሬዚዳንት ዮአን ላፖርታ የአዲሱ ‘ስፖቲፋይ ካምፕ ኑ’ ስታዲየም ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ለክለቡ ባለውለታ ሊዮኔል ሜሲ ልዩ የክብር መርሃግብር ለማዘጋጀት ማቀዳቸውን ይፋ አድርገዋል።

ላፖርታ እንደገለጹት የአዲሱ ስታዲየም ግንባታ መጠናቀቅን ተከትሎ ከሚከናወኑ ዋና ዋና መርሐግብሮች አንዱ ለሜሲ የሚገባውን ታላቅ የክብር ስንብት ማዘጋጀት ነው።

እንደ ማርካ ዘገባ ይህ ውሳኔ ሜሲ በ2021 ከክለቡ በድንገት ሲለቅ ያጣውን ተገቢ የክብር ስንብት በካምፕ ኑ ስታዲየም በሺዎች በሚቆጠሩ ደጋፊዎች ፊት እንደገና የሚያገኝበት አጋጣሚ ይፈጥራል ተብሏል።

ስታዲየሙ የፈረንጆች 2028 አመት ላይ እንደሚጠናቀቅ ታሳቢ ተደርጓል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_11_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here