ካርሎስ ባሌባ ወደ ሜዳ ለመመለስ በከፍተኛ ጉጉት ላይ መኾኑን ማይክልካሪክ ገለጹ።
የማንቼስተር ዩናይትዱ አሠልጣኝ ማይክል ካሪክ አዲሱ ካሜሩናዊ አማካይ ካርሎስ ባሌባ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ጨዋታዎች ለመመለስ ትልቅ ፍላጎት እና ጉጉት እንዳደረበት ገልጸዋል።
በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከብራይተን በ65 ሚሊዮን ፓውንድ ማንቼስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው ባሌባ በቅድመ-ውድድር ዘመን ባጋጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት ምክንያት የመጀመሪያ ጨዋታውን ሳያደርግ ቆይቷል። አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ የተጫዋቹን ሁኔታ አስመልከተው በሰጡት አስተያየት የተጫዋቹን ጠንካራ ስብዕና እና ተነሳሽነት ማድነቃቸውን ስካይ ስፖርት አስነብቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



