በዓለም የጎዳና ላይ አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ውጤት 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች።

0
95
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በዴንማርክ ኮፐንሀገን የተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል።
በሁለቱም ፆታዎች በሦሥት ርቀቶች በተካሄደው በዚሁ ውድድር ኬንያ በ3 ወርቅ ፣3 ብርና 1 ነሐስ በድምሩ በ7 ሜዳሊያዎች በቀዳሚነት አጠናቅቃለች።
ኢትዮጵያ ደግሞ 1 ወርቅ፣ 2 ብር እና 1 ነሐስ በድምሩ 4 ሜዳሊያዎችን በማግኘት 2ኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ 1 ወርቅና 1 ነሐስ ሜዳሊያ ያገኘችው ኤርትራ 3ኛ ኾና ጨርሳለች።
ኢትዮጵያ በውድድሩ ሜዳሊያዎቹን ያገኘችው በልቅና አምባው በ5 ኪሎ ሜትር ሴቶች ወርቅ፣ በፍሬወይኒ ኃይሉ በሴቶች 1 ማይል ብር፣ በወንዶች ግማሽ ማራቶን የቡድን ውጤት ብር አና በሴቶች ግማሽ ማራቶን የቡድን ውጤት ነሐስ ነው።
በአጠቃላይ በዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ውድድር የምንጊዜም የደረጃ ሠንጠረዥም ኬንያ እና ኢትዮጵያውያን በቀዳሚነት ተቀምጠዋል።
ኬንያ 55 ወርቅ፣ 34 ብር እና 23 ነሐስ በድምሩ 112 ሜዳሊያ በማግኘት፤ ኢትዮጵያ ደግሞ 17 ወርቅ፣ 26 ብር እና 21 ነሐስ በአጠቃላይ 64 ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ሮማንያ አና ኤርትራ 3ኛ እና 4ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የውድድሩ አዘጋጆች መረጃ ያመለክታል።
በኃይሌ አበራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here