ሁሉንም ጨዋታዎች በማሸነፍ ድንቅ ብቃት ላይ የሚገኘው የማንቸስተር ሲቲ ጉዞ በ ሰንደርላንድ ይገታ ይኾን?

0
111

 

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ዛሬ አራት ተጠባቂ ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲኾን ከእነዚህ ጨዋታዎች መካከል ማንቸስተር ሲቲ ከ ሰንደርላንድ ቀን 10፡00 የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

በአሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ የሚመራው እና በውድድር ዓመቱ ያደረጋቸውን ሁሉንም ጨዋታዎች በማሸነፍ ድንቅ ብቃት ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ሲቲ በኢቲሃድ ስታዲየም ሰንደርላንድን ያስተናግዳል።

ማንቸስተር ሲቲዎች በታሪክ ከሰንደርላንድ ጋር ባደረጓቸው ያለፉት 11 ጨዋታዎች በሙሉ ተሸንፈው የማያውቁ ሲኾን፤ ለአሠልጣኝ ሬጂስ ሌ ብሪስ 100ኛ ጨዋታቸውን በሚመሩበት በዚህ መርሐ-ግብር ሰንደርላንድ በኢቲሃድ ስታዲየም ድል አስመዝግቦ የማያውቅበትን ታሪክ ለመቀየር ይጫወታል።

ማንቸስተር ሲቲዎች በቅጣት ምክንያት ፊል ፎደንን የማያሰልፉ ሲኾን፣ ጄሬሚ ዶኩ ከጉዳት አገግሞ ተመልሷል። በሰንደርላንድ በኩል ሬኒልዶ በቅጣት፣ ሀቢብ ዲያራ እና ሮሜን ሙንድሌ በከባድ ጉዳት ከጨዋታው ውጭ ኾነዋል።

ሌላው ጨዋታ ቦርንማውዝ ከሊቨርፑል ቀን 10፡00 የሚያደርጉት ጨዋታ ሌላው ተጠባቂ ጨዋታ ነው።

አንዶኒ ኢራዮላ ሊቨርፑልን እየመሩ የቀድሞ ክለባቸውን ቦርንማውዝን በቪታሊቲ ስታዲየም ይገጥማሉ። ሁለቱ ቡድኖች ባደረጓቸው የመጨረሻ 8 የእርስ በእርስ ግንኙነቶች 23 ግቦች መቆጠራቸው ጨዋታው በከፍተኛ ግብ የታጀበ ሊኾን እንደሚችል ይጠቁማል።

ሁጎ ኤኪቲኬ፣ ኮኖር ብራድሌይ እና ፌዴሪኮ ኪዬዛ በጉዳት ምክንያት ለሊቨርፑል ግልጋሎት የማይሰጡ ሲኾን፤ በቦርንማውዝ በኩል አሚን አድሊ እና ኤሊ ጁኒየር ክሩፒ በጉዳት ከሥብሥብ ውጭ ኾነዋል።

በሌላ የዕለቱ የፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር ቀን 10፡00ላይ ሊድስ ዩናይትድ በኤላንድ ሮድ ስታዲየም ክሪስታል ፓላስን የሚያስተናግድ ይኾናል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_10_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here