የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያ ጨዋታው አቻ ተለያየ፡፡

0
67

 

የሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር በታንዛኒያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በውድድሩ በመጀመሪያው ምድብ ከአስተናጋጇ ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሩዋንዳ ጋር አድርጎ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይቷል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ቀጣዩን እና የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን በመጀመሪያ ጨዋታዋ ሩዋንዳን ካሸነፈችው ታንዛኒያ ጋር የፊታችን ቅዳሜ የሚያደርግ ይኾናል፡፡

በዚሁ የሴካፋ ዞን ከ20 ዓመት በታች ውድድር ከሦሥቱ ምድቦች በቀዳሚነት የሚያጠናቅቁ ሦሥት ሀገራት እና ጥሩ 2ኛ የኾነ አንድ ቡድን ወደ ግማሽ ፍጻሜ ያልፋሉ፡፡

ለፍጻሜ የሚደርሱ ሁለት ሀገራት ደግሞ በጋና አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች እግር ኳስ ዋንጫ ተሳታፊ ይኾናሉ፡፡

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_07_2019_ዓ_ም

በኃይሌ አበራ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here