ኢንተር ማያሚ ትናንት ምሽት የሜክሲኮውን ክለብ ክሩዝ አዙልን 2 ለ 0 በማሸነፍ የ2026 የካምፒዮነስ ዋንጫ ሻምፒዮን ኾኗል። ክለቡ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜም ይህንን ዋንጫ አግኝቷል።
ይህ ዋንጫ በየዓመቱ በሜጀር ሊግ ሶከር አሸናፊ እና በሜክሲኮ ሊጋ ኤምኤክስ ሻምፒዮን መካከል የሚደረግ ፍልሚያ ነው።
በዚህ ጨዋታ ላይ ሊዮኔል ሜሲ በጭንቅላት በመግጨት የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥሯል። ይህች ግብ ሜሲ ለኢንተር ማያሚ ያስቆጠራት 100ኛ ግቡ ኾና በታሪክ ተመዝግባለች።
ሜሲ በተጨማሪም ካሴሚሮ በ81ኛው ደቂቃ ላይ ላስቆጠራት ግብ ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል።
ይህ ድል ለኢንተር ማያሚ በታሪኩ 5ኛውን ይፋዊ ዋንጫ ያስገኘለት ሲኾን ለሊዮኔል ሜሲ ደግሞ በዘመኑ ያነሳው 49ኛ የዋንጫ ስኬቱ ኾኖ ተመዝግቧል።
አዲሱ የክለቡ ዋና አሠልጣኝ ክሪስቲያን ኪሊ ጎንዛሌዝ ኢንተር ሚያሚን በመሩበት የመጀመሪያ ጨዋታቸውም ዋንጫ አግኝተዋል።
እኝህ አሠልጣኝ እና የክለቡ የከፍተኛ ድርሻ ባለቤት ዴቪድ ቤካም ሊዮኔል ሜሲ የዘንድሮው ባላንዶርን ማሸነፍ የሚገባው እርሱ ነው የሚል ሃሳብ ከጨዋታው በኋላ ሰጥተዋል።
በ39 ዓመቱ ያስመዘገባቸው ስኬቶች ከግምት ገብተው ሽልማቱ የሜሲ ሊኾን ይገባል ብለዋል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_07_2019_ዓ_ም
በሰኢድ ኢብራሂም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



