‎አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በመኾን ተመረጡ።

0
78
‎‎የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 18ኛ መደበኛ እና የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እየተካሄደ ነው።
‎ዛሬ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በባለፉት 8ዓመታት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት የነበሩት እና ብቸኛ ዕጩ በመኾን ቀርበው የነበሩት አቶ ኢሳያስ ጅራ በድጋሜ ተመርጠዋል።
‎ለሦሥተኛ ጊዜ የተመረጡት አቶ ኢሳያስ ጅራ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት የሚመሩ ይኾናል።
‎በአጠቃላይ ከ88 መራጮች መካከል 81 መራጮች አቶ ኢሳያስ ጅራን መርጠዋል።
ኮሚሽነር አለሙ ነገራ ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት በመኾን ተመርጠዋል።
በሌላ በኩል 11 ክለቦች ዛሬ በተደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ባለመገኘታቸው ድምጽ ሳይሰጡ ቀርተዋል።
በባዘዘው መኮንን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here