የ2027/2028 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር የፍጻሜ ጨዋታ በአልያንዝ አሬና ስታዲየም እንደሚደረግ የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር አስታውቋል።
የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ ሜዳ የኾነው አልያንዝ አሬና ለሦሥተኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታን የሚያስተናግድ ይኾናል፡፡
ከዚህ ቀደም አልያንዝ አሬና እ.ኤ.አ 2012 እና 2025 የሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ተደርጎበታል።
ከዚህ በተጨማሪም የ2028/2029 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በባርሴሎናው በካምፕ ኑ ስታዲየም እንደሚካሄድ ታውቋል።
ካምፕኑ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታን ለሦሥተኛ ጊዜ የሚያካሂድ ይኾናል፡፡
ካምፕኑ ከዚህ በፊት እ.ኤ.አ 1989 እና 1999 የፍጻሜ ጨዋታን አስተናግዶ ነበር።
የ2026/2027 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በአትሌቲኮ ማድሪዱ በስታዲዮ ሜትሮፖሊታኖ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡
በዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



