ናይሮቢ እና ሙኒክ የዓለም ሻምፒዮናን እንዲያስተናግዱ ተመረጡ፡፡

0
62
የዓለም አትሌቲክስ የ2029 እና የ2031 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዘጋጅ ከተሞችን ይፋ አድርጓል፡፡
የዓለም አትሌቲክስ የ2029 እና የ2031 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን የሚያዘጋጁ ከተሞችን በቡዳፔስት ባደረገው ሥብሠባ ይፋ ያደረገ ሲኾን የኬንያዋ ናይሮቢ እና የጀርመኗ ሙኒክ ውድድሮቹን በበላይነት እንዲያዘጋጁ ተመርጠዋል።
በዚሁ መሠረት ናይሮቢ የ2029 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን እንድታዘጋጅ የተመረጠች ሲኾን፣ ይህም ታላቁ ውድድር በአፍሪካ አህጉር ሲካሄድ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደርገዋል።
የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዝዳንት ሰባስቲያን ኮ ኬንያ በስፖርቱ ያላትን የጎላ ታሪክ እና ያቀረበችውን አሳማኝ መሰረተ ልማት እና ስፖርት ወዳድነትን አድንቀዋል።
በሌላ በኩል የ2031 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዘጋጅ ኾና የተመረጠችው ሙኒክ ናት፡፡
ይህም ውድድሩ እ.ኤ.አ በ2009 በበርሊን ከተካሄደ በኋላ ወደ ጀርመን ሲመለስ የመጀመሪያው ነው።
ጀርመን በ2022 በኦሊምፒክ ስታዲየም ያዘጋጀችውን የአውሮፓ ሻምፒዮና ጨምሮ ዋና ዋና ውድድሮችን በብቃት ማስተናገድ ለመመረጧ በምክንያትነት ተነስተዋል፡፡
ቀጣዩ የ2027 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በቻይና ከፈረንጆቹ መስከረም 10 እስከ 19/ 2027 ይከናወናል፡፡
በሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here