28 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያየ ርቀት ይወዳደራሉ።
ተጠባቂው የወንዶች 3 ሺህ መሰናክል ከኢትዮጵያ ሳሙኤል ፍሬው፣ ገመቹ ጎዳና፣ አብርሀም ስሜ እና ሀይለማርያም አማረ ይሳተፋሉ።
በሉዛን ውድድር ላይ አስደናቂ ፉክክርን በማሳየት ያሸነፈው ገመቹ ጎዳና ርቀቱን በ31 ነጥብ እየመራ ካለው ሞሮኮዋዊዉ ሱፊያን ኢል ባካሊ ጋር የሚያደርጉት ፉክክር ተጠባቂ ነው።
በሴቶች 1500ሜ በ24 ነጥብ የምትመራው ብርቄ ሀየሎም፣ ከሀገሯ ልጆች ፅጌ ድጉማ፣ ሳሮን በርሄ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ፣ ሀረገወይን ካላዩ፣ ወርቅነሽ መሰለ እና አስቴር አሬሬ ጋር ትፎካከራለች።
በ5000ሜ ሴቶች በርካታ አትሌቶች ይሳተፋሉ። ለአሸናፊነትም ቅድመ ግምትን ኢትዮጵያውያን ወስደዋል።
አለሺኝ ባወቀ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ፣ ልቅና አምባው፣ ሰናይት ጌታቸው ፣ ማርታ አለማየሁ፣ መዲና ኢሳ፣ ሂሩት መሸሻ፣ ሀዊ አበራ፣ ፋንታየ በላይነህ፣ ብርነሽ ደሴ፣ አይናዲስ መብራቱ፣ ሚዛን አለም፣ የኔዋ ንብረት፣ መልክናት ውዱ እና አሳየች አይቼው ከተሳታፊዎች መካከል ናቸው።
ሌላው ተጠባቂ ውድድር ደግሞ በወንዶች 5000 ሺህ ሜትር ነው።
አዲሱ ይሁኔ፣ ቢኒያም መሀሪ፣ መዝገቡ ስሜ፣ ካሀሪ ቤጂጋ እና ኩማ ግርማ ከአንድሬስ አልምግሪንና ከ ብርሀኑ ባለው ጋር የሚያደርጉት ፉክክር ይጠበቃል ።
በሴቶች 800 ሜትር ሳይዳ ፀሀየ እና ንግስት ጌታቸው ተሳታፊ ናቸው።
ዳናይት ሲሳይ
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



