የ2026/27 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ድልድል ዕጣ ዛሬ በፈረንሳይ ሞናኮ ይወጣል።

0
83
36 ክለቦች በአራት የዕጣ ምድቦች ተከፍለው በአዲሱ የውድድር ስርዓት የሚጫወቱትን ተጋጣሚዎች ያውቃሉ።
እንግሊዝ እና ስፔን እያንዳንዳቸው በአምስት ክለቦች ሲወከሉ ጀርመን እና ጣሊያን አራት አራት ክለቦችን በመድረኩ ያሳትፋሉ፡፡
እያንዳንዱ ምድብ ዘጠኝ ክለቦችን በውስጡ የያዘ ሲሆን ፓሪስ ሴንት ጄርሜን፣ ሪያል ማድሪድ፣ ባየርን ሙኒክ፣ ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ሲቲ፣ አርሰናል፣ ባርሴሎና፣ ኢንተር ሚላን እና አትሌቲኮ ማድሪድ በመድረኩ ባላቸው ኮፊሸንት መነሻ በምድብ አንድ ተደልድለዋል፡፡
ሁሉም ክለቦች ስምንት ተጋጣሚ ክለቦች ይደርሷቸዋል፡፡
ዛሬ ምሽት 2፡00 ላይ በሚወጣው ድልድል መሰረት በተከታታይ ሁለት አመት ተመሳሳይ ክለቦች በአንድ ሜዳ ተገናኝተው ከነበረ ለሶስተኛ ጊዜ እርስ በርስ በዚያው ሜዳ እንዳይጫወቱ ይደረጋል፡፡
ለምሳሌ ሊቨርፑል ሪያል ማድሪድን በአንፊልድ እንዲሁም ኢንተር ሚላን አርሰናልን በሳንሴሮ እንዲያስተናግዱ አይፈቀድላቸውም፡፡
የ2026/27 የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በማድሪድ ከተማ ሪያድ ዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲዬም በግንቦት ወር መጨረሻ ይደረጋል፡፡
ብሩህ ውበት
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here