ዮሚፍ ቀጀልቻ የግማሽ ማራቶን አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዘገበ።

0
52
በአርጀንቲና ርዕሰ መዲና በሁለቱም ፆታዎች የተካሄደው የቦነስ አይረስ ግማሽ ማራቶን ውድድር ከደቂቃዎች በፊት ተጠናቋል።
በወንዶች ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ 56 ደቂቃ 51 ሰከንድ በማሸነፍ አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዝግቧል።
ዮሚፍ ክብረወሰኑን ያሻሻለው በ29 ሰከንድ ሲኾን ከዚህ በፊት ክብረወሰኑ ተይዞ የነበረው እ.አ.አ 2024 ላይ በኡጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ ነበር።
ዮሚፍ ቀጀልቻ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት መኾኑም ይታወቃል። በዛሬው የቦነስ አይረስ ግማሽ ማራቶን በሴቶችም ድሉ ከኢትዮጵያዊያን አልወጣም።
ፎይተን ተስፋዬ በ1 ሰዓት ከ03 ነጥብ 57 ሰከንድ በቀዳሚነት ማጠናቀቋን ወርልድ አትሌቲክስ ዘግቧል።
ሀይሌ አበራ
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here