በደቡብ አሜሪካ በድምቀቱ የሚታወቀው የአርጀንቲና ቦነስ አይረስ የ21 ኪሎ ሜትር የግማሽ ማራቶን ውድድር ነገ ይካሄዳል።
በግማሽ ማራቶኑ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ለክብረወሰን ይጠበቃሉ።
በግማሽ ማራቶን በአለም ሁለተኛው ምርጥ ሰአት ያለው ዮሚፍ ቀጀልቻ በዮጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ የተያዘውን የቦታውን ክብረ ወሰን ያሻሽላል ተብሎ የሚጠበቅ አትሌት ነው።
ዮሚፍ በወንዶቹ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ሲሆን በለንደን ማራቶን ደግሞ ከ2 ሰዓት በታች በመግባት ታሪክ ሰርቷል።
ሌሎቹ የሀገሩ ልጆች ገመቹ ዲዳ፣ ታደሰ ወርቁ፣ በረከት ነጋ እና ገብረፃዲቅ አብርሀ ለአሸናፊነት ጉልበት እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
በሴቶች ዘርፍ በግማሽ ማራቶን ፈጣን ሰአት ያላት ፎቴን ተስፋዬ ለክብረወሰን እንደምትሮጥ አዘጋጆቹ ሲያሳውቁ
በኬንያዊቷ ሩት ቼፕጌቲች የተያዘውን የቦታውን ክብረ ወሰን እንደምታሻሽል ይጠበቃል::
በ2025 በርሊን ግማሽ ማራቶን እና በ ባርሴሎና በተካሄደው የ2026 ማራቶን አሸናፊ የሆነችው እና በታሪክ የዓለማችን 3ኛዋ ፈጣን የግማሽ ማራቶን ሯጭ የሆነችው ፎይተን ተስፋዬ ከድል በላይ ክብረወሰን እንደምታሻሽል ተጠብቋል።
ወጣቷ አትሌት ሜላት ስዩም የቡድን ስራ እንደምታግዝ ይጠበቃል ።
ዳናይት ሲሳይ
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



