ቶተንሀም የ22 አመቱን የመስመር አጥቂ ለማስፈረም 75 ሚሊዬን ፓውንድ ለመክፈል ወስኗል።
ተጨዋቹ በማንቸስተር ሲቲ ያለፈው አመት ቆይታው በቂ የመሠለፍ እድል አለማግኘቱ ሌሎች ክለቦችን እንዲያማትር አድርጎታል።
ቶተንሀም ባለፈው አመት በሳቪንሆ ላይ ፍላጎት ነበረው። ሆኖም ከ12 ወራት በኋላ ሊሳካለት ተቃርቧል።
የህክምና ምርመራው እንዳጠናቀቀ የረጅም ጊዜ ኮንትራት ለቶተንሀም ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።
የሮቬርቶ ዲዘርቪው ቶተንሀም ከዚህ ቀደም አማካኝ ክፍሉን ለማጠናከር 185 ሚሊዬን ፓውንድ ወጭ በማድረግ ሳንድሮ ቶናሊ እና ማቲያስ ፈርናንዴዝ ማስፈረሙ ይታወሳል።
በመለሰ ግዛቸው
#ባሕር_ዳር፡ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



