20ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ከመስከረም 09/2019 ዓ.ም እስከ መስከረም 26/2019 ዓ.ም ይካሄዳል።
ስድስት የአዲስ አበባ ከተማ ክለቦች እና ከሁለት ተጋባዥ የክልል ክለቦች በድምሩ ስምንት ክለቦች በዘንድሮው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ተሳታፊ እንደሚኾኑ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መቻል፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ መድን በውድድሩ ተሳታፊ ክለቦች ናቸው። ጋሞ ጨንታ እና አዳማ ከተማ በተጋባዥነት የሚሳተፉ ይኾናል።
የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን እዳስታወቀው ውድድሩን ለማዘመን እና ፌዴሬሽኑን በገቢ ለማጠናከር የውድድሩ ኮሜርሽያል መብት ለሦሥት ዓመታት በሚዘልቅ ውል በ45 ሚሊዮን ብር መሸጡን ገልጿል።
ፌዴሬሽኑ ከቫርዳስ/vardas እና ኒዮ/neo/ ጋር በተፈራረመው ስምምነት ነው ውድድሩ ለሦሥት ዓመታት በ45 ሚሊዮን ብር የተሸጠው። ስምምነቱም ከዘንድሮው ውድድር ጀምሮ ተግባራዊ ይኾናል ነው የተባለው።
ዘጋቢ፦ባዘዘው መኮንን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



