ለ24 ተኛ ጊዜ በተካሄደው እና በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው የሲድኒ ማራቶን ኢትዮጵያዊው አዲሱ ጎበና 2 ሰአት 04 ደቂቃ 42 ሰከንድ በመግባት የቦታው ክብረ ወሰን በማሻሻል አሸንፏል።
ባለፈው ዓመት በሀይለማርያም ኪሮስ ተይዞ የነበረውን የቦታውን ክብረወሰን ከአንድ ድቂቃ በላይ በማሻሻል ነው ያሸነፈው።
ጭምዴሳ ደበሌ 2ኛ ፣ ጀማል መኮንን 5ኛ ሲወጡ ያለፈው ዓመት አሸናፊ ሀይለማርያም ኪሮስ ደግሞ 6ኛ ደርጃን ይዞ አጠናቋል።
በሴቶች ከውድድሩ በፊት የተጠበቀችው ኬንያዊቷ ፒርስ ጅፕችርችር አሸናፊ ሆናለች።
ኢትዮጵያዊያኑ ሹሬ ደምሴ፣ ሄቨን ሀይሉ ፣መሰረት አበባየሁ ከ3ኛ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
ዳናይት ሲሳይ



