ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የፊንላንድ ፓቮ ኑሚሪሚ አሕጉራዊ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል።

0
8

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1957 የተጀመረው እና የወርቅ ደረጃ የተሰጠው ፓቮ ኑሚሪሚ አሕጉራዊ ውድድር ዛሬ በፊንላድ ይካሄዳል።

ኢትዮጵያውያን ይደምቁበታል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ውድድር እውቅ አትሌቶችንም እንደሚያሳትፍ ነው የሚጠበቀው።

በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ከሁሉም ተወዳዳሪዎች ፈጣን ሰዓት ያለው እና በቤት ውስጥ የ3 ሺህ ሜትር የኢትዮጵያ ክብረወሰን ባለቤት ጌትነት ዋለ ተሳታፊ ነው።

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የባለፈው ዓመት የሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ አሸናፊው አብርሃም ስሜም በውድድሩ ተጠባቂ ኾኗል።

እንደ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ከኾነ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ኬና ቱፋ ተሳታፊ ስትኾን፣ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ፈጣን ሰዓት ያላት አለምናት ዋለም ተጠባቂ ኾናለች፡፡

በምስጋናው ብርሃኔ

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት_አትሌቲክስ #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here