የጆዜ ሞሪንሆ ጥብቅ ሕጎች በሪያል ማድሪድ ቤት

0
69

 

በበርካታ አነጋጋሪ አስተያየታቸው እና ተግባራቸው የሚታወቁት አሠልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ በሪያል ማድሪድ ተጫዋቾች ዘንድ ይታዩ የነበሩ ያልተገቡ ልማዶችን ለመለወጥ ጥብቅ የዲስፕሊን ደንቦችን መተግበር መጀመራቸውን ዲያሪዮ ኤኤስ የተሰኘ ድረገጽ ዘግቧል።

በክለቡ ውስጥ ጠንካራ ሥነ-ሥርዓትን ለመመለስ አሠልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ተግባራዊ ያደረጓቸውን ሕጎች ስንመለከት፦

የትኛውም ተጫዋች አመጋገቡ ላይ ገደብ ተጥሎበታል። ተጫዋቾች የፈለጉትን የመመገብ ነፃነት እንዳይኖራቸው የገቱት አሠልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ የክለቡ የሥነ-ምግብ ባለሙያ እያንዳንዱን የምግብ ዝርዝር በጥብቅ እና በታቀደ መልኩ እንዲቆጣጠር አዘዋል።

ሌላው ሕግ ወደ ልምምድ ዘግይቶ መምጣት በጭራሽ አይፈቀድም፤ አንድ ደቂቃ እንኳ ዘግይቶ የደረሰ ተጫዋች በቅጣት ለብቻው በጂም ውስጥ ልምምድ እንዲሠራ ይደረጋል፤ ምንም ዓይነት ምህረት የለም ነው ያሉት።

ከጉዳት የሚያገግሙ ተጫዋቾች ከክለቡ ውጭ ከግል አሠልጣኞች ጋር ማገገም እንደማይቻልም ጥብቅ መመሪያ ሰጥተዋል። ሁሉም የማገገም ሂደት በክለቡ የሕክምና ሠራተኞች ቀጥተኛ ቁጥጥር ብቻ ይከናወናል ነው ያሉት።

በበርካታ አነጋጋሪ አስተያየታቸው እና ተግባራቸው የሚታወቁት ሞሪንሆ በሳንቲያጎ በርናባው የነበረውን የቆየ ጠንካራ የዲስፕሊን ባሕል እንደገና ለመመለስ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ነው ያብራሩት።

#AMECO #ስፖርት

#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_03_2018_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here