የቀድሞው የሜክሲኮ ብሔራዊ ቡድን እና የማንቸስተር ዩናይትድ አጥቂ ቺቻሪቶ ኤርናንዴዝ ስለ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ስለ ፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን የአማካይ ክፍል ሥብሥብ የሰጠው አስተያየት በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ኾኗል።
ቺቻሪቶ ለስካይ ስፖርት በሰጠው አስተያየት ፖርቱጋል በዓለም ዋንጫው ላይ አስደናቂ የአማካይ ክፍል ሥብሥብ የነበራት ቢኾንም ለቡድኑ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቂ የግብ ዕድሎችን አለመፍጠሯን ኮንኗል።
ቺቻሪቶ ኤርናንዴዝ በሰጠው አስተያየት “ፖርቱጋል በዓለም ዋንጫው ላይ በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ የአማካይ ክፍሎች አንዱ ነበራት። እንደ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ያሉ ምርጥ ተጫዋቾችን የያዘው ሥብሥብ ለክርስቲያኖ 10 ዕድል እንኳ መፍጠር አልቻሉም” ብሏል።
የሮናልዶን እጅግ አስደናቂ የግብ ማግባት ብቃት ያደነቀው ቺቻሪቶ ኤርናንዴዝ “ሮናልዶ ያገኘው ሁለት ዕድል ብቻ ነበር ሁለቱንም ግን ወደ ግብነት ቀይሯቸዋል” ሲል ተናግሯል።
ይህን የቺቻሪቶ አስተያየት ተከትሎ በስፖርት ተንታኞች እና በደጋፊዎች ዘንድ አዲስ ክርክር አስነስቷል።
በምሥጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



