ባሕር ዳር፡ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ፊፋ በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ ጥቅም ላይ የሚውል ውሳኔዎችን የሚያፈጥን አዲስ “ሰሚ አውቶሜትድ” የኦፍሳይድ ቴክኖሎጂ አስተዋውቋል።
ይህም ዘግይቶ የሚነሳውን የረዳት ዳኞች ባንዲራ ታሪክ ሊያደርገው ተቃርቧል።
አዲሱ ቴክኖሎጂ አንድ ተጫዋች ከ10 ሳንቲ ሜትር በላይ ከኦፍሳይድ ውጭ ሲኾን ለረዳት ዳኛው ወዲያውኑ የድምጽ ምልክት ያሰማል።
ይህም ቀደም ሲል በክለቦች ዓለም ዋንጫ ከተሞከረው እና 50 ሳንቲ ሜትር ሲኾን ብቻ ምልክት ከሚሰጠው ቴክኖሎጂ በእጅጉ የተሻሻለ ነው።
ዘቹዝን ደይ እንደዘገበው ይሁን እና ቴክኖሎጂው እጅግ የተቀራረቡ ጥቃቅን የኦፍሳይድ መስመሮችን የመለየት ውስንነት ስላለበት የመጨረሻው ውሳኔ አሁንም በዋናው ዳኛ እጅ ላይ እንደሚኾን ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !


