በወልድያ ከተማ ለብዙኃን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ትኩረት ተሰጥቷል።

0
41

 

ወልድያ: ግንቦት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ የከተማዋን የልማት ሥራዎች መመረቅ አስመልክቶ የጎዳና ላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ አካሂዷል።

ውድድሩ የአካል ብቃት አንቅስቃሴ፣ የአምስት ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር እና የብስክሌት ውድድርን ያካተተ ነበር።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አሠልጣኝ ሳሙኤል ሞገስ የዚህ አይነት የጎዳና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በሳምንት ወይም በሁለት ሳምንት አንድ ቀን ቢደረግ የኅብረተሰቡን የስፖርት ተነሳሽነት ያሳድጋል ብሏል።

ይህም ጤናማ ማኅረሰብ ለመፍጠር እና ብቃት ያለው ትውልድ ለመገንባት ሚናው ጉልህ መኾኑን ነው ያወሳው።

ሌላኛው በሩጫ ውድድሩ እንደኛ የወጣው ወጣት ተክቶ ጌታዬ የሩጫ ውድድር መካሄዱ ታዳጊዎች አቅማቸውን ለመፈተሽ እና ተተኪ አትሌቶችን ለማብቃት ዕድል ይከፍታል ነው ያለው።

በብስክሌት ውድድር ቀዳሚ የነበረው ብስክሌተኛ ክንዱ አበባው የብስክሌት ስፖርት በወልድያ ከተማ የተለመደ አለመኾኑን ተናግሯል።

በከተማው 10 ልጆች ነን ስፖርቱን የምንሠራው ያለው ብስክሌተኛ ክንዱ ስፖርቱ እንዲለመድ ውድድሮች ሊዘጋጁ ይገባል ብሏል።

የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ነፃነት አምበሳው ውድድሩ የከተማዋን የልማት ሥራዎች መመረቅን አስመልክቶ የተዘጋጀ መኾኑን ለአሚኮ ተናግረዋል።

በከተማዋ በሳምንት አራት ቀን በየቀጣናው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ይደረጋል ያሉት ኀላፊዋ እንደዚህ በተደራጀ መልክ በየወሩ በአደባባይ ለማካሄድ መታቀዱንም አስረድተዋል።

#አሚኮ_ዜና #የጎዳናስፖርት_ወልድያ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here