ኢትዮጵያ የ2027ቱን የዓለም አቀፍ ስፖርት ጋዜጠኞች ጉባኤ ለማስተናገድ ተመረጠች።

0
42

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ የ89ኛውን የዓለም አቀፍ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር (ኤአይፒኤስ) ጉባኤ በ2027 እንድታስተናግድ በስዊዘርላንድ ሉዛን በተካሄደው ስብሰባ በሙሉ ድምጽ ተመርጣለች። በታሪካዊው ጉባኤ ላይ ከ300 በላይ ዝነኛ ጋዜጠኞች፣ የፊፋ፣ የካፍ እና የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ መሪዎች በአዲስ አበባ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ ዝግጅት የሀገሪቱን ገጽታ ከመገንባት ባለፈ፣ ወጣት ጋዜጠኞች ዓለም አቀፍ ተሞክሮ እንዲቀስሙ እና የስፖርት ሚዲያው በኢኮኖሚ እንዲጠናከር ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር አስታውቋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here