በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ይጫወታል።

0
63
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ 32ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ማንቸስተር ዩናይትድ በኦልድ ትራፎርድ ስታድየም ሊድስ ዩናይትድን ያስተናግድል።
ማንቸስተር ዩናይትድ በደረጃ ሰንጠረዡ ሦሥተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ማንቸስተር ዩናይትድ የዛሬውን ጨዋታ ድል ካደረገ የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ዕድሉን ከፍ ያደርጋል።
በአንጻሩ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ 15ኛ ላይ የሚገኘው ሊድስ ዩናይትድ ከወረጅ ቀጣና ስጋት ለመራቅ ጨዋታውን የሚያደርግ በመኾኑ ለማንቸስተር ዩናይትድ ፈታኝ እንደሚኾን ይጠበቃል።
በማንቸስተር ዩናይትድ በኩል በቅርቡ ኮንትራቱን ያራዘመው ሀሪ ማጓየር በቀይ ካርድ፤ ማቲያስ ዴሊት እና ፓትሪክ ዶርጉ በጉዳት ከጨዋታው ውጭ ናቸው።
በጉዳት ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ርቆ የቆየው ሊሳንድሮ ማርትኔዝ ለጨዋታው ዝግጁ መኾኑ ለማይክል ካሪክ ቡድን መልካም ዜና ኾኗል።
ጆ ሮደን፣ አንቶን ስታክ እና ዳንኤል ጀምስ በሊድስ ዩናይትድ በኩል በጉዳት አይሰለፉም።
ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር በኤላንድ ሮድ ግጥሚያቸው አንድ አቻ መለያየታቸው ይታወሳል። ባለፉት 15 ዓመታት ማንቸስተር ዩናይትድ በሊግ ጨዋታ በሊድስ ተሸንፎ አያውቅም።
ጨዋታው ምሽት 4:00 ላይ ሰዓት ይደረጋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here