ባሕር ዳር: ሚያዝያ 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሁለት ክለቦችን ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንደሚያሳድግ ይጠበቃል። የ2018 የውድድር ዘመን ምድብ “ሀ” የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ፍፃሜያቸውን ሲያገኙ ጅማ ስታዲየም ላይ ቡራዩ ክፍለ ከተማን የገጠመው ጋሞ ጨንቻ 3ለ0 አሸንፎ 41 ነጥቦችን በመያዝ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።
ደሴ ከተማ የሚገኝበት ምድብ “ለ” ላይ ደግሞ ሁለተኛውን ክለብ ለመለየት በቀጣይ ቀናት በሚካሄዱ ጨዋታዎች የሚለይ ይኾናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



