የክርስቲያኖ ሮናልዶ ልጅ ድንቅ የቅጣት ምት ግብ አስቆጥሮ የአባቱን የደስታ አገላለጽ አሳየ።

0
48

የፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ልጅ የኾነው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጁኒየር በተሰለፈበት ጨዋታ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል።

ታዳጊው ተጫዋች በጨዋታው አንድ አስደናቂ የቅጣት ምት ግብ ያስቆጠረ ሲኾን፣ ግቡን ካስቆጠረ በኋላም የአባቱ መለያ የኾነውን የእጅ ምልክት በማሳየት ደስታውን ገልጿል።

ይህ የክርስቲያኖ ጁኒየር እንቅስቃሴ የአባቱን ፈለግ እየተከተለ መኾኑን በድጋሚ ያሳየ ልዩ አጋጣሚ ኾኗል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_19_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here