ኢትዮጵያ የአፍሪካ መስማት የተሳናቸው እግር ኳስ ውድድርን ልታስተናግድ ነው።

0
81

የአፍሪካ መስማት የተሳናቸው እግር ኳስ ውድድር ከኅዳር 20/2019 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።

በወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ከኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው አሶሴሽን ጋር በመተባበር በሚዘጋጀው በዚህ ውድድር ላይ ከ18 በላይ የአፍሪካ ሀገራት ይሳተፋሉ።

ውድድሩ የሀገሪቱን የስፖርት ዲፕሎማሲ ከማጎልበቱም ባለፈ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ለማጠናከር እና የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ለመገንባት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

የመስማት የተሳናቸው እግር ኳስ መደበኛውን የፊፋ ሕግ የሚከተል ቢኾንም፣ ለተጫዋቾች ደኅንነት እና የዕይታ ተደራሽነት ሲባል ልዩ መመሪያዎች አሉት፦

#የመስሚያ_መሳሪያ_ክልከላ፦ ተጫዋቾችን ከጉዳት ለመጠበቅ ወደ ሜዳ ከመግባታቸው በፊት የመስሚያ መሳሪያቸውን ማውለቅ ይጠበቅባቸዋል።

#የባንዲራ_ምልክት፦ የመሐል ዳኛው ጨዋታ ለማስጀመር ወይም ለማስቆም ፊሽካ በሚነፋበት ቅጽበት፣ ተጫዋቾች በዕይታ እንዲረዱ በተመሳሳይ ጊዜ ባንዲራ ያውለበልባሉ።

#የአምስት_ዳኞች_ሥርዓት፦ ተጫዋቾች ወደ የትኛውም አቅጣጫ ቢመለከቱ የጨዋታ መቆም እንዳያመልጣቸው ከግብ መስመሮች ጀርባ ሁለት ተጨማሪ ረዳት ዳኞች በባንዲራ በመታገዝ ጨዋታውን ይመራሉ።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_18_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here