የባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም ዛሬ በአጼዎቹ ይደምቃል።

0
24

ፋሲል ከነማ ከ ኢትዮጵያ መድን በ7ኛ ሳምንት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ የሚያደርጉትን ጨዋታ ታላቁ የባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም ያስተናግዳል።

አጼዎቹ እና እንግዳው ቡድን ኢትዮጵያ መድን እስካሁን ዘጠኝ ጊዜ ያክል ተገናኝተዋል።

በዚህ ግንኙነታቸውም ሦሥት ጊዜ አጼዎቹ ሲያሸንፉ ሁለት ጊዜ ደግሞ ኢትዮጵያ መድኖች ድል ቀንቷቸዋል። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ የተለያዩበት ጨዋታ ነው።

በእነዚህ ግንኙነቶች ዘጠኝ ግቦች መረብ ላይ አርፈዋል። አምስቱ ግቦች በኢትዮጵያ መድን መረብ ላይ ሲያርፉ አራቱ ግቦች ደግሞ በአጼዎቹ መረብ ላይ ነው ያረፉት።

ይህም የሁለቱ ቡድኞች ግንኙነት የግብ እጥረት እንዳለበት አማላካች ነው።

ጉዳዩ ዛሬስ ፈረስ በሚያስጋልበው ምቹው የባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም ማን ያሸንፋል የሚለው የሚጠበቅ ነው። ምላሹን ግን የ10፡00 ጨዋታ ይሰጠናል።

በጨዋታው ማን ያሸንፋል ሀሳባችሁን አጋሩን?

በሌላ የሊጉ ጨዋታ፦

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሀድያ ሆሳዕናን አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ 9፡30 የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል።

#አሚኮ #ስፖርት

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_19_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here